አንዲትም ሴት በወር አበባ ድህነት ወደኃላ መቅረት የለባትም!

      “ሴቶች በዓለም ሁሉ እጅግ ጠንካራ ሰዎች መሆናችን የታወቀ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡
የወርአበባ የሴቶች ጉዳይ ብቻ ሊሆን አይችልም! የመላው አለም እንጂ፡፡ያደግኩበት ማህበረሰብ በዓመፅ የሚፈስ ደምን እንደ ንፁህ ደምይመለከታል፣ግን ሰላማዊ እና ተፈጥሯዊ ደምአሰቃቂ እና እሳፋሪ ነው፡፡ስለ ሰብአዊ መብቶች እየተነጋገርን ነገር ግን ስለ የወር አበባ መነጋገር የሚከብደን ከሆነን ሰብአዊ መሆናችን የቱ ጋር ነው? ፡፡እኛ ሴቶች  የአለም መስረት እና አንጥረኞች እንደ መሆናችን እኛም ከሰብዓዊ መብት ተቋዳሽ መሆን አለብን!፡” Mahlet zeleke

ንቅናቄ ለምን አስፈለገ?

ይህ ንቅናቄ በዋነኛነት ያስፈለገው በሀገራችን የሚገኙ የመመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በስነ- ተዋልዶ ጤና እና የወር አበባ እና ንፅህና አጠባበቅ ዘርፍ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሻሻል እና የወር አበባም ሴቶችን የምንገነባበት እንጂ የምናንጏጥትበት ያለመሆኑን ;ወጣት ና ታዳጊ እንደመሆናቸው ስለወሲብ እና አባላዘር በሽታዎች ተገቢውን ግንዛቤ ያሉበትን እድሜ ባማከለ መንገድ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ታስቦ የተነደፈ እና በተግባር ላይ የዋለ ነው:: በተጨማሪም ሴት ተማሪዎች ከእናቶቻችን እሴቶቻቸውን መማራቸው; ጥሩ ስነ ልቦና እንዲያዳብሩ እና ባህልን ቀማወቅ እሴትን ከመጠበቅ በተጨማሪ ሌሎች የክህሎቶችም ምማሪያቸው አስፈላጊ ሆኖ ስለታመነበት ነው::

ሥራዎቻችን በምስል

የቅርብ ስራዎቻችንን ለማየት “ስራዎቻችን” ገፅ ይመልከቱ:: በማህበራዊ ሚድያ @icare_power_period @weeafrica_ ብለው ይመልከቱ::

Follow us on : facebook Instagram

Translate »