#እኔም_ያገባኛል #Icare

#ICARE #እኔም_ያገባኛል ንቅናቄ በ ማህሌት ዘለቀ የሴቶች እና ልጃገረዶች ድጋፍ የአለም አቀፍ እንደራሴ; በpower period የኢትዮጵያ ተጠሪ አማካኝነት በሂልተን አዲስ እ.አ.አ በMarch 6 launch ተደርጏል:: 
ንቅናቄውም ሴት ጃገረዶችን ለከፍተኛ ትምህርት እንዳይበቁ ከሚያደርጏቸው መሰናክሎች ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ድጋፍ ማድረግ ነው::
ሴት ልጃገረዶችን ለከፍተኛ ትምህርት እንዳይበቁ ከሚያደርጏቸው መሰናክሎች በዋነኛነት የሚጠቀሱት ያለ እድሜ ጋብቻ: ጠለፍ; ተገዶመደፈር  እንዲሁም ለከፍ በይበልጥ የሚነሱ ሀሳቦች ሲሆኑ: የስነተዋልዶ  እና የወር አበባ ትምህርቶችን በተገቢው መንገድ ለልጃገረዶች መድረስ አለባት ብለን ተነስተናል:: 
ስለሰብዓዊ መብቶች ስናወራ ስለ የወርአበባ እንዲሁም ስለ ተፈጥሯዊ ለውጦች የማናወራ ከሆነ ሰብዓዊነታችን ምኑ ላይ ነው?   
እኛ ሴቶች የአለም መሰረቶች እና እንጥረኞች እንደ መሆናችን እኛም ከሠብዐዊ መብቶች ተቋዳሽ መሆን መቻል አለብን::                             
የምንኖርባት አለም ክፉ ናት: ኮንዶም በነፃ በሚታደልበት አለም የወርአበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሶችንን ይሽጥባታል::  ወሲብ ምርጫ ሲሆን የወር አበባ ግን የተፈጥሮ ግዴታ ነው!
   ከአነስተኛ ቤተሰብ የሚወጡ ልጃገረዶች በየቀኑ እየተሰቃዩ ነው:: ይህ ደሞ እንደ ሠብዐዊ መብትን መግደፍ ነው::  
ከ10 ሴት አንድዋ በወር አበባ ምክንያት ከትምህርቷ ትስተጏጎላለች:: ይህ ሴቶችን ማስተማር ሀገር ማስተማር  ነው እያለ እየተናገረ ካለ ማህበረሰብ ጋር የሚፃረን ነው:: 
ጥቂትማ ይባሉ እንስትእህቶች የንፅህና መጠበቂያ  ቁሶችን መግዛት ይቸግራቸዋል:: ወጪውም እየናረ እየሄደ ነው:: ከኢኮኖሚ እንዲሁም ከእውቀት ማነስ በአንድ ፓድ እረጅም ሰአታትን ይቆያሉ::  ይህን እንደ መፍትሄ ልናነሳ ምንችለው ተገቢውን ትምህርት ማድረስ ና ቁሶችን በማቅረብ ነው::

 ስለዚህም ንቅናቄያችን
🔴ስለ ወር አበባ እንዲሁም የሴቶች ጤና አጠባበቅ ና የስነተዋልዶ ትምህርቶችን በመጀመሪያና ሁለተኛ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ወርዶ ግንዛቤን ማስጨበጥ::

🔴ለእህቶቻችን የንፅህና መጠበቂያ ለሚያስፈልጋቸው: ቁሶቹን በማሰባሰብ እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ማዳረስ::

🔴ሴቶች በብዛት በሚገኙባቸው ትምህርት ቤቶች ከመንግስትና ባለሀብቶች ጋር በመተባበር የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን በመፀዳጃ ቤቶች አካባቢ ማመቻቸት::

🔴ዋናው አላማችን  የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን እዚሁ ሀገር በማምረት ለሴት እህቶቻችን ድጋፍ መሆን::  

ከላይ እንደጠቀሰው በአሁኑ ሰአት የንፅህና መጠበቂያ ቁሶች ዋጋቸው እየናረ ነው:: ይህ የተፈጥሮ ግዴታ እንጂ ውዴታ አይደለም!::  

“ይህ ካንፔን ወይም ንቅናቄ በዋናነት ከዚህ በታች የተገለጹትን ጠቀሜታዎች ለተሳታፊዎች፣ ለትምህርት ቤቶች ፣ ለከተማው ብሎም ለሀገራችን ይሰጣል ተብሎ ይታሰባል፡

✓ በትምህርት ቆይታቸው ተማሪዎቹ ስለ-ስነ ተዋልዶ ጤና ያላቸውን ግንዛቤ እንዲሁም ስለ ንፅህና አጠባበቅ ያላቸውን እውቀት እንዲያሳድጉ ይረዳል፡፡

✓ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በተማሪዎች መካከል የመቀራረብ እና የመደጋገፍ ባህልን ይበልጥ ያሳድጋል፡፡

✓ ተማሪዎች እና የትምህርት ቤቶቹ ማህበረሰብ አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት የትውውቅ መድረክ ይፈጥራል፡፡

✓ በተማሪዎች ዘንድ ለ ወር አበባ የሚሰጠውን የተዛባ አመለካከት መቀየር እና ግንዛቤ መስጠት ያስችላል፡፡

✓ ሴት ተማሪዎች እችላለሁ የሚለውን መንፈስ እንዲላበሱ እና የሚደርስባቸውን ጫና እና ጥቃት መከላከል የሚያስችላቸውን ስነ ልቦና ለመፍጠር ይረዳል፡፡

✓ የክፍለከተማው ጤና ቢሮ ፣ የሴቶች ጉዳይ፣ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎችም ባለድረሻ አካላት በተናጥል ከሚያደርኩት ጥረት በተጨማሪ በጋር የሚሰሩበትን መድረክ ያመቻቻል፡፡

✓ ወጣት ሴቶች ታዳጊ ሴቶችን የሚያነቃቁበት እና የሚደግፉበትን መድረክ ያመቻቻል፡፡

✓ እርስ በርስ በመጠያየቅ አለሁልሽ ሚለውን ስሜት መፍጠር ያስችላል፡፡

✓ ስለ አካለዊ ለውጥ በነፃነት ከሴት ጏደኞቻቸው እንዲሁም አቻቸው ጋር የሚያወሩበትን የሚማማሩበት ስለ ጤንነታቸውን ከህክምና ባለሙያዎች ድጋፍን የሚያገኙበት ንቅናቄ ነው::

✓ የንፅህና መጠበቂያ በማጣት አንዲት ሴት ልጅ ከትምህርቷ መስተጓጎል የለባትም!!! የወር አበባ የተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ሊያተርፉበት የማይገባ የተፈጥሮ ፀጋ መሆኑን ማስገንዘብ፡፡

✓ ከዚህ በተጨማሪ የንፅህና ቁሳቁሶችን ከተለያዩ አካላት ድጋፍን በመጠየቅ ለሚያስፈልጋቸው እህቶች ማድረስ:: በዘላቂነትም እዚሁ እምርትን ከአነስተኛ ቤተሰብ ለሚወጡ ተማሪዎች በነፃ መግዛት ለሚችሉ እጅግ በጣም ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ማቅረብ:: ብሎም ለሴቶች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ አካላት የስራ እድል መፍጠር::

~ በማዕከላቱም እሴቶቻችን ከእናቶቻችን የምንማርበት መድረክ እኛም ለታናናሾቻችን የምናስተምርበት ትስስርን መፍጠር”

ሴቶች በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያላቸውን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያሉባቸውን ችግሮች መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ።

በሥራና ክህሎት ሚኒሰቴር ስር ካሉ ቴክኒክና ሙያ ስለጠና ኮሌጆች አንዱ በሆነው የሎጎ ሀይቅ ቴክኒክና ሙያ ስለጠና ኮሌጅ የሴት ሰልጣኞች የስልጠና ማቋረጥ ምክንያትን ለማወቅ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ሴት ሰልጣኞች ስልጠናቸውን እንዲያቋርጡ ከሚያደርጋቸው ምክንያቶች አንዱ የግል ንጽህን መጠበቂያ መሳሪያ እጥረት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ይህ የተገለፀው በዛሬው ዕለት በሚኒስቴር መስሪያ በቱ ወስጥ በተዘጋጀ የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው፡፡

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር በከር ሻሌ (ዶ/ር) እንደገለጹት የሎጉ ሃይቅ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የሰልጣኝ ሴት ተማሪዎችን ችግር ከሥርዓተ ጾታ እንዲሁም አጠቃላይ የመንገስትና የዘርፉ አቅጣጫ ጋር በማያያዝ ማንነው የሚፈታው ብለው ሳያስቡ ችግሩን በመለየታቸው በሚኒስቴር መ/በቱ ስም የኮሌጁን ዲን የሆኑትን አቶ ተመስግን ጸጋየን አመስግናዋል፡፡

ለችግሩ መፍትሔ የሰጡትን እና ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ድጋፍ ያደረጉትን #Icare #እኔም_ያገባኛል፥ ጀግኒት እንቅስቃሴዎች እና አደይ ፓድስ የወር አበባ መቀበያ አምራች ድርጅትን ሚኒስትር ዴኤታው ያመሰገኑ ሲሆን ይህ ተግባር የሴት ሰልጣኞችን ችግር ለመፍታት የሚያስችል አንድ መንገድ የከፈተ በመሆኑ ይህንን ዕድል በማስፋት ለሌሎች ኮሌጆችም በድጋፍ መልክ ብቻ ሳይሆን ኮሌጆች ራሳቸው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ እንደመሆናቸው መጠን አምርተው ጭምር እዚው ችግሩን መፍታት እንዲችሉ በዕቅድ አቅጣጫ እንድናካትትና የሚኒስቴር መ/ቤቱን የሥርዓተ ጾታ እይታችንን ያሰፋ በመሆኑ ትልቅ ክብርና አድናቆት አለኝ በለዋል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሀንስ በበኩላቸው እንደገለጹት “ይህን ችግር ለመፍታት ያነጋገሯቸው ተቋማት አይኬር ፣ጀግኒት ኢትዮጲያ እና አደይ ፓድ አምራቾች ድርጅት ሀላፊዎች ለጉዳዩ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት የ100 ሴት ሰልጣኞችን የሁለት አመታት ችግር የሚፈታ ድጋፍ አድርገዋል::” ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

አያይዘውም “ሴቶች በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያላቸውን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያሉባቸዉን ችግሮች መፍታት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡ “በአገራችን 72% በመቶ የሚሆኑት ሴቶች በአስደንጋጭ ሁኔታ የንጽህና መጠበቂያ አያገኙም ” ከሚለው ጥናት በኋላ በመነሳት ተማሪዎች ላይ ትኩረት ያደረገ በተለይም ሴቶች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ሁሉን አቀፍ የወር አበባ መቀበያ ብርቄ ባልዲን እንደተረከቡ ገፀዋል ፡፡

ይህም “ብርቄ” በሚል ስያሜ የተጀመረ እንቅስቃሴን በማካሄድ ለሁለት ዓመት የሚያገለግል የንጽህና መጠበቂያ ፓድ ሳሙና እና የውስጥ ሱሪ በማዘጋጀት በ2014 ዓ.ም ለ33600 ( ለሰሳ ሶስት ሽህ ስደስት መቶ) ሴት ተማሪዎች አድረሰናል ያሉት የአደይ ፓድ ንጽህና መጠበቂያ ማመረቻ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሚካል ማሞ ናቸው፡፡

ይህን ተግባር ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር በመስራታችንና ድጋፉን ለሎጎ ሐይቅ ቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ኮሌጅ በማድረጋችን እኔም ሆንኩ አጋሮቻችን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ድጋፉ የተድረጋላቸው የሎጎ ሐይቅ ቴክኒክና ሙያ ማስልጠኛ ኮሌጅ ዲን አቶ ተመስገን ጸጋየ ድጋፉ ስለተደረገላቸው አመስግነው የሴት ሰልጣኞች ችግር ዘርፍ በዙ ችግር መሆኑን አውስተው በቀጣይ ይህን መሰልና ሌለች ድጋፎች እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads Every girl deserves access to menstrual hygiene products.”
Birqe was delivered at gebeya dar Kebele school. Thank you for your continuous donations🤎. We thank Dr Adugna Getahun for delivering birqe in hawasa with his team! #girls #pads #menstrualhygiene #education #Birqe #keepgirlsinschool #birqedistribution

Instagram: @icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads “Every girl deserves access to menstrual hygiene products.” 250 Birqe was given to government school around saris Addis Abeba. Thank you for your continuous donations🤎 it’s keeping our sisters in school!


@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads “Every girl deserves access to menstrual hygiene products.” 60 Birqe was given to Gebeya far school in Hawasa. Thank you for your continuous donations🤎. We thank Dr Adugna Getahun for delivering birqe in Hawasa city with his team!


Thank you for your commitments on keeping girls in school.
No Girl Left behind Period! PERIOD🩸
To fill in the gap where there are opportunities to change the realities for girls, y’all we came up with a BirQePeriodKit aiming to raise awareness and avail menstruation products to combate school-absenteeism and dropout among girls in Ethiopia by preparing a Period kit that consists of Reusable sanitary pads, underwear, towels, soap and such. Tiffaniandlu & Ohginababe (Instagram account @tiffaniandlu @ohginababe) been supporting the movement for so long!
We take time to appreciate the support they are giving us.
(WE ARE VERY SORRY FOR Not sharing photos recently due to on the conflict in Ethiopia it was very hard to get photos and videos after distributing to rural areas and out of Addis )
Access to menstrual products IS a NECESSITY and NOT a LUXURY. It should be every girl’s RIGHT to feel clean, confident and capable during her bleeding.
KeepherinSchool #NOGirlLeftBehindPeriod #KeepingGirlsInSchool #BiQePeriodKit #JegnitIcare #icare #እኔምያገባኛልጀግኒት
@icare_power_period @jegnitethiopia. @adey_pads
እናመሰግናለን!! Best Wester Hotel
በሴቶች ወር ማህበራዊ ሃላፊነታችሁን ለመወጣጥ “አንዲትም ተማሪ በወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ መደናቀፍ የለባትም!” ብላችሁ ብርቄን ለተማሪዎች በማድረሳችሁ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው!

@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads
ሀገራችን ላይ ባለው ሁኔታ ብርቄ ለተማሪዎች ከደረሰች በኃላ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ሲደር ለእናንተ ለማሳየት ብንጓጓም በኔትዎርክ እና በተለያዩ ችግሮች ፎቶዎች እና ቪድዮዎች በግዜ ሳይደርሱን ቆይተዋል:: እንደሁልግዜው የተቀሩት ሲደርሱን እናጋራለን!
በግሩፕ ሆናችሁ የለገሳችሁ
የማህበራዊ ሚድያ ድህረ-ገፃቻችሁን እንድንጠቀምበት የፈቀዳችሁ ሁሉ ምስጋናችንን ለማቅረብ የብርቄ ባልዲን በድርጅታችሁ ሎጎ እንዲሁም በስማችሁ አድርገን አድርሰናል::
አብራችሁን ስለነበራችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን::
ዮፍታሄ ሾው፥ ሮያሊቲበአቢጌል ፥ሄላዝቢውቲ ፥ዮኒማኛ ፥ዲጄ ወንድም፥ እንቧ ፋሚሊ፥ @dopelifestylefitness202

@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads

“በወር አበባ ምክንያት አንድም ሴት መሰቃየት አይገባትም !
በሞዴስ ውድነት እንዲሁም በግንዛቤ እጦት ምክንያት ብዙ ሴት እህቶቻችን እየተጨቆኑ ይገኛሉ ። ነገሩ እንደምናስበው ቀላል አይደለም!::
ተፈጥሮኣዊ የሆነውን የወር አበባ እሚሸማቀቁበትና አላማቸውን እሚያደናቅፍ ሆኖባቸዋል በዛ ላይ ከዚህ የኑሮ ውድነት ጋር አንድ ሞዴስ እስከ 70 ብር ይሸጣል ::
ይህን ችግር ለመቅረፍ icare , jegnit እና Adey pads አብረውበመተባበር “ብርቄ” ፈጥረዋል
እኛም ደግሞ የተቻለንን ብርቄ በማበርከት አንድም ሴት ከ ት/ት ቤት እንዳትቀር እንደግፉቸው።”

አርቲስት ሊድያና ሰለሞን እናመሰግናለን!!

ዮፍታሄ ሾው እና ሀበሻን ዌብ በእናንተ አጋዥነት 200 ተማሪዎች ለሚመጡት 2 አመታት ከትምህርት ገበታቸው ላይ ይቆያሉ! እናመሰግናለን ::


Every girl deserves access to menstrual hygiene products.”
80 Birqe was given to Brave Hearts
Thank you Marta Borena 🤎
#girls #pads #menstrualhygiene #education #keepinggirlsinschool #donations #thanksgiving

@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads
በርቺ Talk ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን!!
ብርቄ በሚዛን ቴፒ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች ደርሳለች ::
@berchitalk ብርቄን በምናሰባስበት ወቅት ስላገዛችሁን እናመሰግናለን::
በሚዛን ቴፒ ለሚገኙ 150 ሴት ተማሪዎች ደርስዋል::
ይቀጥላል….!!!
ስለተሳተፋችሁ እናመሰግናለን!!
@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads
በ ቦሌ ገርጂ እና ማርች 8 ትምህርትቤቶች ለሚገኙ 200 ሴት ተማሪዎች #ለእህቴ በተሰኘው እንቅስቃሴ በኩል ድጋፍ አድርገናል::
@le_ehite ለተማሪዎች በኃላፊነት ስላደረሳችሁ እናመሰግናለን!::
@icare_power_period @jegnitethiopia @adey_pads
ብርቄ በአፋር ለሚገኙ 300 መቶ ተማሪዎችበጎፈቃደኞች በቦታው ተገኝተው አድርሰዋል::ይህ እንዲሆን ከጎናችን ለነበራችሁሁሉብምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ::
ብርቄን በምናሰባስብበት ወቅት እኔ እያለው ተማሪዎች ከትምህርታቸው አይስተጉዋጎሉም ብላችሁ ስለሰጣችሁ እንዲሁም ስላስተባበራችሁ እናመሰግናለን::
በእናንተ ምክንያት እነዚህ ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አይቀሩም::

Translate »