እኔም ያገባኛል ንቅናቄ

ንቅናቄውም ሴት ልጃገረዶችን ለከፍተኛ ትምህርት እንዳይበቁ ከሚያደርጏቸው መሰናክሎች ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ድጋፍ ማድረግ ነው::
ሴት ልጃገረዶችን ለከፍተኛ ትምህርት እንዳይበቁ ከሚያደርጏቸው መሰናክሎች በዋነኛነት የሚጠቀሱት ያለ እድሜ ጋብቻ : ጠለፍ ; ተገዶ መደፈር እንዲሁም ለከፍ በይበልጥ የሚነሱ ሀሳቦች ሲሆኑ : የስነ ተዋልዶ እና የወር አበባ ትምህርቶችን በተገቢው መንገድ ለልጃገረዶች መድረስ አለባት ብለን ተነስተናል::
ስለ ሰብዓዊ መብቶች ስናወራ ስለ የወር አበባ እንዲሁም ስለ ተፈጥሯዊ ለውጦች የማናወራ ከሆነ ሰብዓዊነታችን ምኑ ላይ ነው?
እኛ ሴቶች የአለም መሰረቶች እና እንጥረኞች እንደመሆናችን እኛም ከሠብዐዊ መብቶች ተቋዳሽ መሆን መቻል አለብን::
የምንኖርባት አለም ክፉናት : ኮንዶም በነፃ በሚታደልበት አለም የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሶችንን ይሽጥባታል:: ወሲብ ምርጫ ሲሆን የወር አበባ ግን የተፈጥሮ ግዴታ ነው!
ከአነስተኛ ቤተሰብ የሚወጡ ልጃገረዶች በየ ቀኑ እየተሰቃዩ ነው:: ይህ ደሞ እንደሠብዐዊ መብትን መግደፍ ነው::
ከ10 ሴት አንድዋ በወር አበባ ምክንያት ከትምህርቷ ትስተጏጎላለች:: ይህ ሴቶችን ማስተማር ሀገር ማስተማር ነው እያለ እየተናገረ ካለ ማህበረሰብ ጋር የሚፃረን ነው::
ጥቂት ማይባሉ እንስት እህቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን መግዛት ይቸግራቸዋል:: ወጪውም እየናረ እየሄደ ነው:: ከኢኮኖሚ እንዲሁም ከእውቀት ማነስ በአንድ ፓድ እረጅም ሰአታትን ይቆያሉ:: ይህን እንደመፍትሄ ልናነሳ ምንችለው ተገቢውን ትምህርት ማድረስና ቁሶችን በማቅረብ ነው:: ስለዚህም ንቅናቄያችን
🔴 ስለወር አበባ እንዲሁም የሴቶች ጤና አጠባበቅ ና የስነ ተዋልዶ ትምህርቶችን በመጀመሪያና ሁለተኛ ሳይክል ትምህርት ቤቶች ወርዶ ግንዛቤን ማስጨበጥ::

🔴 ለእህቶቼ የንፅህና መጠበቂያ ለሚያስፈልጋቸው : ቁሶቹን በማሰባሰብ እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ለማቅረብ ስራዬን ጀምርያለሁ::

🔴 ሴቶች በብዛት በሚገኙባቸው ትምህርት ቤቶች ከመንግስት ና ባለ ሀብቶች ጋር በመተባበር የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን በመፀዳጃ ቤቶች አካባቢ ማመቻቸት::

🔴 ዋናው አላማችን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን እዚሁ ሀገር በማምረት ለሴት እህቶቻችን ድጋፍ መሆን ::

ከላይ እንደጠቀሰው በአሁኑ ሰአት የንፅህና መጠበቂያ ቁሶች ዋጋቸው እየናረ ነው :: ይህ የተፈጥሮ ግዴታ እንጂ ውዴታ አይደለም!::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Translate »