ሴቶችን ለከፍተኛ ትምህርት ማብቃት ሲሆን በዚህ ጉዞ ላይ የሚያጋጥሙትን መሰናክሎች ለመቅረፍ በሙሉ አቅሙ የሚሰራ ንቅናቄ ነው::
ሴቶችን ለከፍተኛ ትምህርት እንዳይበቁ ከሚያደርጏቸው መሰናክሎች አንዱ የስነ ተዋልዶ እና የወር አበባ ትምህርቶችን በተገቢው መንገድ ለልጃገረዶች አለማድረስ ነው::
እኛ ሴቶች በወር አበባችን ግዜ መሠረታዊ ንፅህና መጠበቂያ ፓድ : ቴንፓን : የወር አበባ ፅዋዎች እንዲሁም ተያያዥ ቁሶች ያስፈልጉናል:: ‘ሴቶች በአለም ሁሉ እጅግ ጠንካራ ሰዎች መሆናችን የታወቀ እና የማይካድ ሀቅ ነው:: የወር አበባ የሴቶች ጉዳይ ብቻ ሊሆን አይችልም:: የኛ ማህበረሰብ በአመፃ የሚፈሰውን ደም እንደ ንፁህ ነገር ግን ሰላማዊ እና ተፈጥሮአዊ የሆነን ደም እንደ አሰቃቂ እና ነውር ይመለከታል::
ስለ የወር አበባችን ማውራት
ሴቶችን ማብቃት ሀገርን መገገንባት ነው! ሴቶች በማህበረሰቡ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ ግልፅ ነው:: ሴቶችን ለማብቃት ትልቅ ደረጃ ላይ ለማድረስ የተለያዩ አስተሳሰቦችን እንዲህም እንደነውር የሚታዩ የተፈጥሮ ፀጋዎች; የስነተዋልዶ ትምህርት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በእኛ በኩል የሚጠበቀውን ለ አመለካት ለውጥ ለማምጣት: እየተንቀሳቀስን ነው::
ስለ ሰብዓዊ መብቶች ስናወራ ስለ የወር አበባ እንዲሁም ስለ ተፈጥሯዊ ለውጦች የማናወራ ከሆነ ሰብዓዊነታችን ምኑ ላይ ነው?” እኛ ሴቶች የአለም መሰረቶች እና እንጥረኞች እንደመሆናችን እኛም ከሠብዐዊ መብቶች ተቋዳሽ መሆን መቻል አለብን:: የምንኖርባት አለም ክፉናት : ኮንዶም በነፃ በሚታደልበት አለም የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ቁሶችንን ይሽጥባታል:: ወሲብ ምርጫ ሲሆን የወር አበባ ግን የተፈጥሮ ግዴታ ነው! ከአነስተኛ ቤተሰብ የሚወጡ ልጃገረዶች በየ ቀኑ እየተሰቃዩ ነው:
ታስፈልጊናለሽ! ታስፈልገናለህ! ታስፈልጉናላችሁ!
የስነ-ተዋልዶ ትምህርትን የወር አበባ ምንነት ግንዛቤን በበቂ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ለማድረስ ስልጠናዎችን በመስጠት: ለመነጋገር ; ችግሮችን በጋራ ለመፍታት; ታሪክሽን ለማሰማት እና ከታሪክሽ ለመማር; ለማስተማር , ቁሳቁሶችን ገዝተው በመለገስ እንዲያግዙን; ምክሮችን እንዲለግሱን ምንም አይነት የበጎ ፈቃድ ድጋፎ የሚበረታታ ስለሆነ እርሶም የእዚህ መልካም ተግባር አካል መሆን ከፈለጉ በገፃችን በተጠቀሱት አድራሻዎች ያነጋግሩን
