ቀድሞ መዘጋጀት, የአካልን እና የአካልን ለውጥ በሚገባ መረዳት እንዲሁም በራስ መተማመን, የወር አበባን አቅለን እንድናይ እና የወር አበባችን ላይ በምንሆንበት ግዜ ሳንሳቀቅ ተገቢውን እንቅስቃሴ እንድናደርግ ይረዳናል:: ይህ ትንሽ መፅሐፍ ነገር ግን ብዙ እውቀትን ያዘለ ሲሆን , የወር አበባሽን ማየት ጀመርሽም ;አልጀመርሽም በቂ መመሪያን የሚሰጥ ሲሆን ስለአካላዊ ለውጥ እና ተያያዥ ነገሮችም በበቂ መልኩ ግንዛቤን ያስጨብጣል:: ጮክ ብለን ለማንጠይቃቸው ነገር ግን መልሳቸው ለሚያስፈልጉን ጥያቄዎችም በቂ ማብራሪያ እና ትንታኔን ይሰጣል ! የወር አበባ የሴት ልጅ ጌጥ ; ውበት እና ጤንነት ነው!!