“ንቅናቄው በመጀመሪያ ደረጃ በስነተዋልዶ እና የወር አበባ ምንነት ግንዛቤ እንዲሁም የንፅህና አጠባበቅ ስልጠናን እና የወር አበባ መቀበያ ቁሶችን ማዳረስን ጨምሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቅዶች እና አላማዎች የያዘ ነው::
I.በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የጀመርነውን የስርአተ ፆታ ትምህርት እንዲሁም የወር አበባ ምንነት ግንዛቤን ሰፋ ባለ እቅድ ለተማሪዎች በፕሮግራም በህክምና ረዳቶች እና ባለሙያዎች በመታገዝ በተገቢው መንገድ ለተማሪዎች ማድረስ እየሰራን ነው፡፡
II. በሴቶች ማእከሉም አነስተኛ ቤተ መፅሐፍት: ለስልጠና እና ለመወያያ መድረኮች የሚሆን ቦታ ማዘጋጀት: የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ማስቀመጫ ማዘጋጀት እንዲሁም ሴት ተማሪዎች በወር አበባቸው ግዜ የሚያርፉበትን ቦታ ማዘጋጀት ያካተተ ነው::
III. ሴት ተማሪዎች እርስ በእርስ አጋርነታቸውን እና የእችላለሁ መንፈስን የሚገልጹበትን ስርአት መቅረፅ::
IIII. በትምህርት ቤቶቹ በትምሀህርታቸው ውጤታማ የሆኑ ሴት ተማሪዎችን እንዲሁም የክበቡ አባላትን መሸለም እና ማበረታታት፡፡
V. ተመሳሳይ ክበባትን በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ማስፍፍት እንዲሁም በገጠሪቱ ክፍለሀገራት በመግባት ወንድሞችን ና አባቶችን በበቂ ሁኔታ ስለ ወር አበባ ግንዛቤ ማስጨበጥ::
VI ለአካላዊ ለውጥ ታዳጊዎችን ቀድሞ ማዘጋጀት, የአካልን እና የአካልን ለውጥ በሚገባ እንዲረዱ እንዲሁም በራስ መተማመናቸው , የወር አበባን አቅለው እንዲያዩ እና የወር አበባቸው ላይ በሚሆኑበት ግዜ ሳይሳቀቁ ተገቢውን እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይረዳል::”